ዘመናዊ ተማሪዎች ከቀድሞ ትውልዶች በተለየ ሁኔታ ይማራሉ፤ ምክንያቱም፡

  • መረጃ በሁሉም ቦታ ይገኛል
  • ቴክኖሎጂ ሐሳብን ያቀናል( technology shapes thinking)
  • የትኩረት ጊዜ አጭር ነው
  • ወሳኙ ክህሎት ነው እንጂ ማስታወስ አይደለም
  • መማር በንቃት፣ በተገቢነት እና በተሳትፎ መሆን አለበት

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የ21ኛው ክፍለ ዘመን ትምህርት መሠረታዊ ስርዓቶች(መርሆዎች) በክፍልና ውጪ መጠቀም የተሻለ ትምህርት ለማቅረብ ያስችላልና እንጠቀምበት። ይህም ማለት ውጤታማ እውቀትንና ክህሎትን የሚያስጨብጥ ትምህርት እነዚህን መርህ ተከትሎ መሰጠት አለበት ማለት ነው፡፡ እንዲያ ሲሆን በ21ኛ ክፍለ ዘመን በማህበረሰቡ በብቃትና በንቃት መሳተፍና  አስተዋፅኦ ማበርከት የሚችሉ ትውልድ መቅረፅ ይቻላል ለማለት ነው፡፡

1. ተማሪዎች በንቃት (Active Learning) ቢማሩ የተሻለ ይማራሉ

  • ተማሪዎች በመስማት ብቻ አይማሩም፤ በመስራት የበለጠ ይማራሉ።

ይህንን መርህ መምህራን  እንዴት ይጠቀሙ:

  • ቡድን ስራ በመስጠት( group work)
  • ፕሮጀክት በማሰራት ማስተማር(Project-based learning)
  • ሙከራዎችን በማሰራት(experiments)
  • ነገሮችን በጥናት እንዲያገኙ በማድረግ( inquiry and discovery)
  • ችግር በመፍታት( problem-solving tasks)
  • በመፍጠር (ቪዲዮ፣ ሞዴሎች፣ ፖስተሮች፣ መልሶች)( learning by creating)

2. ተማሪዎች በትብብር የበለጠ ይማራሉ (አብሮ በመማማር)

በ21ኛ ክፍለ ዘመን ተማሪዎች የሚበቁት በሚከተሉት ሁኔታ ሲማሩ ነው፡

  • ውይይት በማድረግ( discuss)
  • ሲከፋፈሉ( share)
  • እርስ በእርሳቸው ሲማማሩ( teach each other)
  • ተደራድረው ሲስማሙ( negotiate)

ይህንን መርህ መምህራን  እንዴት ይጠቀሙ:

  • አስብ–ጋር–አካፍል (Think–Pair–Share)
  • በትብብር የሚሰራ ስራ በመስጠት
  • እኩያ ትምህርት
  • የቡድን ፕሮጀክቶች
  • የትብብር ዲጂታል መሣሪያዎች (Google Docs, Padlet ወዘተ) በመጠቀም

በትብብር  መማር መግባባት፣ ትኩረት ፣አስተውሎትና( critical thinking ) ማህበራዊ ክህሎትን ለተማሪዎች ያሻሽላል።

3. ተማሪዎች በእውነተኛ ዓለምና በተገቢ መማር  ይፈልጋሉ( Students Need Real-World, Relevant Learning)

  • ተማሪዎች የሚማሩት ይዘት ከሚኖሩት ሕይወት ጋር ተያይዞ ሲሰጥ በተሻለ ሁኔታ ይማራሉ። ይህም ማለት የሚማሩት ነገር በህይወታቸው ውስጥ ትርጉም ያለው መሆኑን ሲረዱ ለትምህርቱ የበለጠ ይነቃቃሉ፣ ምኞትና ፍላጎታቸው ይጨምራል፡፡

ይህንን መርህ መምህራን  እንዴት ይጠቀሙ:

  • ከአካባቢ ምሳሌዎችን መጠቀም
  • እውነተኛ ችግሮችን መጠቀም
  • ኬዝ ስታዲዎች( case studies)
  • ማህበረሰብን መሠረት ያደረገ ትምህርት
  • ትምህርትን ከዕለታዊ ተግባር ማገናኘት

4. ተማሪዎች በመጠየቅና በማስተዋል ይማራሉ( Students Learn Through Critical Thinking and Inquiry)

  • ለ21ኛው ክፍለ ዘመን ተማሪዎች መረጃን መተንተን እንጂ መናገር ወይንም መድገም ወይንም ማስታወስ በቂ አይሆንም ፡፡

ይህንን መርህ መምህራን  እንዴት ይጠቀሙ:

  • ክፍት ጥያቄዎች መጠየቅ
  • “ለምን?” እና “እንዴት?” የሚሉ ጥያቄዎችን እንዲጠይቁ ማበረታታት
  • በመጠየቅና መመለስ የሚሰሩ ስራዎችን በመስጠት (inquiry-based tasks)
  • ተማሪዎች እንዲፈትሹና  ጥናት ማድረግ
  • ሁሉንም መልስ መስጠትን በማቆም

5. ተማሪዎች  ቴክኖሎጂን  እንደ ድጋፍ  ሲጠቀሙ  የበለጠ ይማራሉ( Students Learn Best When Technology Supports Learning )

  • ቴክኖሎጂ መምህር የሚተካ ሳይሆን መሣሪያ ነው።

ይህንን መርህ መምህራን  እንዴት ይጠቀሙ:

  • ትምህርት ቪዲዮዎች
  • ትምህርት መተግበሪያዎች
  • እውነተኛ መሞከሪያ ላብራቶሪዎች
  • ዲጂታል ክፍት ጥያቄዎች (Google Classroom, Kahoot, Quizizz)
  • ሜሊቲ ሚዲያ ማቅረብ
  • ኢ-ትምህርት መድረኮች

ቴክኖሎጂ ተማሪዎች  ትምህርትን በንቃት  እና ቀላል በማድረግ እንዲማሩ እድል ይሰጣል

6. ተማሪዎች ደህንነቱ በተጠበቀና  ደጋፊ ሁነታ ውስጥ የበለጠ ይማራሉ( Students Learn Better in Safe, Supportive Classrooms   )

  • ስሜታዊ ደህንነት የአእምሮ አፈጻጸምን ያሻሽላል።

ይህንን መርህ መምህራን  እንዴት ይጠቀሙ:

  • አዎንታዊ ግንኙነት መመስረት
  • የሚደግፍ አስተያየትና ግብረ መልስ መስጠት
  • የማሸማቀቅና  ቅጣት እንቅስቃሴን መቀነስና ማስወገድ
  • አክብሮት ያለው አካባቢ መፍጠር
  • የእድገት አእምሮን ማበረታታት (“ ማሻሻል ትችላለህ በማለት ማበረታታት”)

ተማሪዎች ደህንነት ሲሰማቸው   ስጋትን መቀበልና  ተሳትፎን መጨመር ይችላሉ።

7. ተማሪዎች በግላቸው  መማር ይችላሉ( Students Learn Through Personalized Learning)

  • ሁሉም ተማሪዎች በአንድ አይነት  ሁኔታ አይማሩም።

ይህንን መርህ መምህራን  እንዴት ይጠቀሙ:

  • ትምህርትን በተለያዩ ሁነታ መስጠት( differentiate instruction)
  • አማራጮችን ማቅረብ (ርዕስ፣ ዘዴ፣ መሣሪያ)
  • ስራዎችን በተማሪ ደረጃ ማስተካከል
  • ቡድን እንደ ሁነታው በማቀያየር መመስረት
  • ግላዊ ግብረ-መልስ መስጠት

ግላዊ መማር የተማሪዎችን መነሳሳት፣ ተሳትፎ  እና ውጤትን ያሻሽላል።

8. ተማሪዎች በተከታታይ ግብረመልስ የበለጠ ይማራሉ( Students Learn Best with Continuous Feedback)

  • ትምህርት ቀጣይነት ያለው ማስተካከልና ድጋፍ ይፈልጋል — የመጨረሻ ውጤት ብቻ አይደለም።

ይህንን መርህ መምህራን  እንዴት ይጠቀሙ:

  • ፈጣን ተከታታይ ሚዘና በመስጠት
  • የመውጫ ማስታወቂያ
  • ክፍት ጥያቄዎች
  • የራስና የእርስ በርስ ሚዘና በማካሄድ
  • ቃላዊ ግብረ-መልስ በመስጠት
  • ዲጂታል ግብረ-መልስ መሣሪያዎችን በመጠቀም

ፈጣን ወይንም ወዲያውኑ ግብረ መልስ መስጠት  ተማሪዎች በእውነተኛ ጊዜ ማሻሻል  እንዲያደርጉ ይረዳቸዋል።

9. ተማሪዎች በፈጠራና በኢኖቬሽን  ይማራሉ( Students Learn Better Through Creativity and Innovation  )

  • ፈጠራ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ከፍተኛው ክህሎት ነው።

ይህንን መርህ መምህራን  እንዴት ይጠቀሙ:

  • የንድፍ ሐሳብን ማበረታታት( encourage design thinking)
  • የፈጠራ የሆነ ውጤትን ማበረታታት  (አፈ-ታሪክ፣ ቪዲዮ፣ ሞዴል፣ ፖስተር) መፍጠርን ማበረታታት
  • ሐሳብን ማበረታታት
  • አርቲና ሜሊቲ ሚዲያን መጠቀም
  • አዳዲስ ሀሳብንና ተነሳሽነትን ማበረታታት

10. ተማሪዎች በጠናማ አእምሮና ሰውነት የበለጠ ይማራሉ

  • እንቅስቃሴ መማርን ያበረታታል ጭንቀት ነገር ግን  መማርን ያቀጭጫል፡፡

ይህንን መርህ መምህራን  እንዴት ይጠቀሙ:

  • በመሀል አእምሮ እረፍት መስጠት
  • እንቅስቃሴ ላይ የተመሰረተ የክፍል ስራ
  • የአእምሮ ስራ (mindfulness (breathing, stretches))
  • የተመጣጠነ የክፍል ውስጥ ሐይል( balanced classroom energy)
  • መልሶ ራስን ለማየት ጊዜ መስጠት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *